Abilu

የ28 ዓመቱ አቢሉ ስለ እራሱ ማወቅ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ አርሶአደር ሲሆን “ያደግኩት እዚህ መሬት ላይ ነው፣ ትንሽ ልጅ እያለሁ አባቴን እዚሁ መሬት ላይ አግዝ ነበር፣ ከብቶችም እጠብቅ ነበር፤ አሁን ላይ የራሴን አነስተኛ ማሳ ተከራይቼ ሽንኩርት፣ በቆሎና ጤፍ (ጥራጥሬ) አበቅላለሁ፤ ይህን አንድ ሄክታር መሬት ከ10 ሰራተኞቼ ጋር በመሆን አለማለሁ፤” ሁኔታው ሁሌም ቀላል አይደለም፣ “አዋሽ ወንዝ ውሃ ይሰጠናል፣ ይህም አዝዕርቴን ለማብቀል ያስፈልገኛል፣ ይሁንና ለወንዙ በእጅጉ ቀርቦ መገኘት ጉዳትም አለው፣ ለሁለት ጊዜያት ሰብሌን በጎርፍ ምክንያት አጥቻለሁ፤ ይህ ማሳ ለእኔ የገቢዬ ምንጭና ህልውናዬ ነው፣ ስለዚህ ሰብሌ በጎርፍ ሲወሰድ ምን ላደርግ እችላለሁ? በማለት ይጠይቃል፡፡

የአቢሉ ታሪክ

ስሜነሽ፣ አቢሉ፣ ጋዲሶ እና ደጎ የአዋሽ ወንዝ ሰዎች መካከል ናቸው፣ በተደጋጋሚ እሷ ወይም እሱ የሚነግሩን እሷ ወይም እሱ ምን እያደረጉ እንዳሉ እና ፕሮጀክቱ በህይወታቸው ላይ ምን ዓይነት ተፅዕኖ እንደሚያመጣ ነው፤