ስለ ፕሮጀክታችን

በአዋሽ ወንዝ ተፋሰስ ላይ የተከናወኑ ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች በተፋሰሱ ውስጥ የተሳለጠና የዘመነ  (የተሻሻለ)የውሃ አስተዳደር፣ የውሃ ጥራት፣ እንዲሁም የውሃ አቅርቦት ተደራሽነት ጉዳዮችን መሰረት አድርገው ሰርተዋል፤ በዚህም ውስጥ በርካታ ባለድርሻዎች ተሳትፈዋል፣ ለአብነት የፌደራልና የክልል መንግስታት፣ ካምፓኒዎች፣ የውሃ ተቋማት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ይገኙበታል፡፡ የእነዚህ ፕሮጀክቶች ዋነኛ ዓላማ በአዋሽ ወንዝ ተፋሰስ ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎች ከወንዙ ውሃ ፍሃዊና ዘለቄታዊ በሆነ መንገድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና የአካባቢው ስነ-ምህዳር እንዲያገግም ማድረግ ነው፡፡

የውሃ እሴት (ዋጋ ትመና)

“የውሃ እሴት/ዋጋ” ላይ ያተኮረው ይህ ፕሮጀክት በአዋሽ ወንዝ ላይ በሚገኘው ንዑስ ተፋሰስ እ.ኤ.አ. ከ2018 እስከ 2024ዓ.ም. እየተተገበረ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ በዋነኛነት የበለጠ ውጤታማ የውሃ አጠቃቀም እንዲኖር እና ያለውን ውሃ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ማሰራጨትን ዓላማ አድርጎ ይሰራል፡፡ በአዋሽ ወንዝ ያለው የውሃ መጠን በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ ይገኛል፣ የዚህም ዋናው ምክንያት ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ ለኢንዱስትሪ እና ለመስኖ እርሻ ስለሚውል ነው፤ በዚህም መነሻ የወንዙ የታችኛው ክፍል በሂደት ሊደርቅ ይችላል፡፡

ሰማያዊ የአዋሽ ክፍፍል / ስምምነት / ፕሮግራም

በሰማያዊ የአዋሽ ክፍፍል / ስምምነት / ፕሮግራም የደች የውሃ ባለስልጣን በጋራ ከኢትዮጵያ መንግስት (የፌደራልና የክልል ተቋማት) ጋር በመተባበር በአዋሽ ወንዝ ተፋሰስ የውሃ አስተዳደር ሥርዓቱን ለማሻሻል የሚሰራ ይሆናል፡፡