Dego Mekanen

ደጎ መኮንን ዕድሜው 52 ዓመት ሲሆን ባለትዳር እና 21 እና 14 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሁለት ልጆች አባት ነው፡፡ በጦር ሰራዊት ውስጥ ካገለገለ በኃላ በአዋሽ ወንዝ ዳርቻ በሚገኘውና ከአባቱ በወረሰው መሬት ላይ ወደ እርሻ ገብቷል፡፡ “በአሁኑ ሰዓት ሁለት የተለያዩ የእርሻ ማሳዎች አሉኝ፣ ከዚህ ውስጥ 0.75 ሄክታር የሚሆነው በመስኖ የሚለማ ሲሆን ሌላኛው 0.75 ሄክታር ግን በመስኖ የሚለማ አይደለም” በማለት ያስረዳል፡፡ ምስጋና ለመስኖ ልማት ይግባውና እሱና ቤተሰቡ ለኑሮ የሚበቃቸውን በቂ ምርት ያገኛሉ፤ ይሁንና የሽንኩርት ምርት በሽታ እና የማዳበሪያ እጥረት አርሶ አደር ደጎ መኮንን እርሻውን አስፋፍቶ እንዳያከናውን አድርጎታል፡፡

የደጎ መኮንን ታሪክ

ስሜነሽ፣ አቢሉ፣ ጋዲሶ እና ደጎ የአዋሽ ወንዝ ሰዎች መካከል ናቸው፣ በተደጋጋሚ እሷ ወይም እሱ የሚነግሩን እሷ ወይም እሱ ምን እያደረጉ እንዳሉ እና ፕሮጀክቱ በህይወታቸው ላይ ምን ዓይነት ተፅዕኖ እንደሚያመጣ ነው፤