በሰላማዊ የአዋሽ ክፍፍል / ስምምነት/ የትብብር ፕሮግራም የደች የውሃ ባለስልጣን በጋራ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር በአዋሽ ወንዝ ተፋሰስ የውሃ አስተዳደር ሥርዓቱን ለማሻሻል የሚሰራ ሲሆን፣ በዚህ ፕሮግራም ሶስት ፕሮጀክቶች ይካተታሉ እነሱም፡-
- የወንዝ ተፋሰስ አስተዳደር ፕላን መተግበር
- የውሃ መረጃ እና የኢንፎርሜሽን ማኔጅመንት ሥርዓቱን ማሻሻል
- የፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት፣ የእንክብካቤ እና የፍሳሽ ውሃ ከመልቀቅ ክፍያ መሰብሰብ ሥርዓት መዘርጋት
ፕሮጀክት 1
የወንዝ ተፋሰስ አስተዳደር ፕላን መተግበር፡
አዋሽ ተፋሰስ ባለስልጣን በአዋሽ ወንዝ ተፋሰስ የውሃ አስተዳደር ተግባራትን ለማከናወን ኃላፊነት ተሰጠው ተቋም ነው፤ ባለፉት ዓመታት የደች የውሃ ባለስልጣን ስትራቴጂክ የወንዝ ተፋሰስ አስተዳደር ፕላን በማዘጋጀት የአዋሽ ተፋሰስ ባለስልጣንን ሲያግዝ ቆይቷል፤ አሁን ደግሞ በዚህ ሂደት ከኢትዮጵያ በርካታ አጋሮችን በማሳተፍ ይህንን ዕቅድ ወደመሬት በማውረድ መተግበር ይገባል፤ የትግበራው ሂደት ሰፊና ውስብስብ የሆኑ ፕሮጀክቶችን የያዘ በመሆኑ በርካታ ትብብሮችን ይፈልጋል፡፡ በዚህ ደረጃ ያለን ዕቅድ መተግበር ለአዋሽ ተፋሰስ አዲስ ነው፤ በሰማያዊ የአዋሽ ክፍፍል / ስምምነት/ የትብብር ፕሮግራም የደች የውሃ ባለስልጣን ለአዋሽ ተፋሰስ ባለስልጣን በሚከተሉት ሁኔታዎች ላይ ድጋፍ ይሰጣል፣ እነሱም የትግበራ ሂደቱን እንዴት ማደራጀት እንደሚገባ፣ ባለድርሻ አካላትንና ሌሎች መንግስታዊ ተቋማትን እንዴት ማሳተፍ እንደሚቻል፣ እንዴት ሂደቱን ለውጥ ማምጣቱን መከታተል እንደሚቻልና ማስተካከያዎችን በሂደቱ ውስጥ ሆኖ ማከናወን እንደሚቻል፣ ስኬታማ የዕቅድ ትግበራ ለማከናወን ባለሙያዎች ምን ዓይነት ክህሎት እንደሚያስፈልጋቸው እና ይህንን አቅም እንዴት ማልማት እንደሚቻል መደገፍ ናቸው፡፡
ፕሮጀክት 2
የውሃ መረጃ እና የኢንፎርሜሽን ማኔጅመንት ሥርዓቱን ማሻሻል (የተፋሰስ ኢንፎርሜሽን ማኔጅመንት ሥርዓት)፡
መረጃና የኢንፎርሜሽን ማኔጅመንት ከፍተኛ ፈተናዎችን እያስከተለ ይገኛል፤ በአሁኑ ሰዓት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች አነስተኛ በሚባል ደረጃ ይገኛሉ፣ ሆኖም ያሉት መረጃዎች አማካይ በሆነ አንድ ቦታ ተሰባስበው አይገኙም፤ አንዳንድ ጊዜም የሚጠፉበትና ሳይተላለፉ የሚቀሩበት ሁኔታ ይስተዋላል፡፡ በሰማያዊ የአዋሽ ክፍፍል / ስምምነት/ የትብብር ፕሮግራም የደች የውሃ ባለስልጣን በተፋሰሱ የሚገኙ አጋሮች መረጃ በተደራጀ መንገድ እንዲያገኙ እንዲሁም የባለድርሻ አካላትን የመረጃ ፍላጎት በተሻለ መንገድ ለማርካት የሚያስችል ድጋፍ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
ፕሮጀክት 3
የፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት፣ የእንክብካቤ እና የፍሳሽ ውሃ ከመልቀቅ ክፍያ መሰብሰብ ሥርዓት መዘርጋት (የኢንዱስትሪ ፍሳሽ ውሃ መልቀቅ ደንብ)
የኢንዱስትሪዎች መስፋፋት፣ ከፍተኛ የመሬት አጠቃቀም (ለእርሻ) እንዲሁም የህዝብ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር የገፀ-ምድር ውሃው በከፍተኛ ደረጃ እንዲበከል አድርጓል፡፡ የሰው ልጆችና የእንስሳት ጤንነት አደጋ ላይ ወድቋል፣ ይህንን ብክለት ለመከላከል የሚያስችል ጠንካራ የህግ ስርዓትም የለም፡፡ በሰማያዊ የአዋሽ ክፍፍል / ስምምነት/ የትብብር ፕሮግራም የደች የውሃ ባለስልጣን የኢትዮጵያ መንግስት ተቋማትን በማሳተፍ እንዴት የፍቃድ አሰጣጥ ሥርዓት መፍጠር እንደሚቻል፣ የኢንስፔክሽንና እንክብካቤ ሥራ ለመስራት እገዛ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ይህ ሥራ ወንዙን ከሚበክሉ አካላት ክፍያ መሰብሰብን ያካትታል፡፡ በሰማያዊ የአዋሽ ክፍፍል / ስምምነት/ የትብብር ፕሮግራም በደች የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በመሰረተ-ልማትና ውሃ ሚኒስቴር የገንዘብ ድጋፍ ይደረግለታል፡፡ የደች የውሃ ባለስልጣን ፕሮግራሙን በተባባሪነት ይተገብራል፡፡